5 Uncoverd windows 10 features
ብዙ ሰዎች የማያቋቸው 5 የ Windows 10 አዳዲስ ገፅታዎች
Windows 10 ላይ ብቻ የምናገኛቸው አዳዲስ እና ጠቃሚ እንዲሁም ስራን የሚያቀላጥፉ ገፅታዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል እርሶም ጊዜ ሳያጠፉ ዛሬውኑ በመሞክር የእርሶ ያድርጉት
1. Snip and Sketch ብዙዎቻችን ስሪናችን ላይ የምናየውን ወይም የመናነበውን ነገር ለጓደኞቻችን ወይም ለምንፈልጋቸው ሰዎች ማጋራት እንፈልጋለን ይህንን ለማድረግ በ sniping tool ስንጠቀም ነበር አሁን ግን snip and sketch መጥቷል ይሄ ከ sniping tool በምን ይሻላል ለምሳሌ አንድን የተወሰነ ስቴፕ መያዝ ብፈልግ sniping tool ማድረግ አይቻልም በ snip and sketch ግን በቀላሉ ማድረግ ይቻላል፡፡
2. Aero Shake በዚህ ወከባ በበዛበት ዘመን ሁላችንም ከአንድ በላይ ስራ መስራታችን የተለመደ ነው በ Windows 10 ላይ ይህንን ስናደርግ ከኋላ የከፍትናቸውን ፕሮግራሞች በአንድ ጊዜ መዝጋት ከፈለግን ሼክ Aero Shake በማድረግ ሁሉንም መዝጋት ወይም ወደ ስክሪኑ ማምጣት እንችላለን፡፡
3. Snap Your Windows Look at multiple windows with split screen ሁለት የተለያየ ዊንዶ ጎን ለጎን ማየት ከፈለግን በ Windows 10 ላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ከላይ ያለውን ቪዲዩ ተመልከቱ፡፡
4. Quick Assist ኮምፒውተሩ ያስቸገረውን ግን ሌላ ቦታ ያለ ሰውን መርዳት በ Windows 10 በጣም ቀላል ነው Quick Assist ገፅታ በመጠቀም ያሉበት ቦታ ሆነው እዛኛው ሰው ኮምፒውተር ላይ በቀላሉ መግባት እና ማስተካከል ይችላሉ፡፡
5. Clipboard History ሁላችንም ኮፒ ፔስት እናደርጋለን ግን አንዳንዴ ኮፒ ካደረግን በኋላ ፔስት ሳናደርግ ሌላ ነገር ድጋሚ ኮፒ እናደርጋለን አሁን ግን ችግር የለም እድሜ ለአዲሱ Win + V ገፅታ በተጨማሪም ሁልጊዜ ፔስት የሚያደርጉትን ነገር ፒን በማድረግ ሁልጊዜ በቀላሉ ፔስት ማድረግ ይችላሉ፡፡ በመጀመሪያ ግን setting ውስጥ ገብተን clipboard option on መሆኑን ማረጋገጥ አለብን